• Home
  • About Us
    • Our Mission and Vision
    • Objectives
    • History
    • Board of Directors
    • Message From CEO
    • Our Leadership Team
  • Investment
    • Sectors We Invest In
    • How We Design Our Investments
    • How We Categorizes Our Investments
    • What Vehicles Does EIH Use?
    • Investment Considerations
    • Investment Process
    • EIH’s Value Proposition
    • Success Stories
  • Portfolio
    • Transport and Logistics
    • Energy and Connectivity
    • Financial Services
    • Mining, Engineering and Chemicals
    • Hospitality
    • Agriculture and Agro-Processing
    • Manufacturing
    • Trading
    • Construction and Real estate
  • Resources
    • Audit Report
    • Annual Report
    • Publications
    • Laws and Regulations
  • More
    • News and Media
    • Gallery
    • Career
    • Tender
    • contact us
qt=q_95

የኢትዮጵያን ቢዝነስ ፕሮሰስ አውትሶርሲንግ (BPO) ኢንዱስትሪን የሚያሳድግ ስምምነት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በሲሲአይ ግሎባል መካከል ተፈረመ

  • November 13, 2026
  • Dagmawi Zeleke

የኢትዮጵያ መንግሥት ስትራቴጂካዊ የኢንቨስትመንት ክንድ የሆነው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (ኢኢሆ) እና በአፍሪካ ቀዳሚው የ ቢዝነስ ፕሮሰስ አውትሶርሲንግ (BPO) ኦፕሬተር የሆነው ሲሲአይ ግሎባል (CCI Global) መካከል የኢትዮጵያን የ ቢዝነስ ፕሮሰስ አውትሶርሲንግ (BPO) ኢንዱስትሪ ዕድገት ለማፋጠን እና ሀገሪቱን በዓለም አቀፍ የዲጂታል አገልግሎት ኢኮኖሚ ውስጥ ያላትን ተሳትፎ ለማስፋፋት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።

ይህ ታሪካዊ ስምምነት ኢኢሆ በአዲስ አበባ እየገነባው ከሚገኘውና ለBPO አገልግሎት ተብሎ ከተዘጋጀው የመሰረተ ልማት ፕሮጀክት ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ኦፕሬተሮች ዘመናዊ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፉ ተቋማት እና የBPO ሥራዎችን በኢትዮጵያ ለመሥራትና ለማስፋፋት የሚያስፈልገውን መሰረተ ልማት ለማቅረብ የተነደፈ ነው።

ፕሮጀክቱ በ26 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ኢንቨስትመንት የሚከናወን ሲሆን፣ በመጀመሪያው ዙር 3,000 መቀመጫዎች የማስተናገድ አቅም ያለው ባለ 4 ፎቅ (G+4) የ BPO ህንፃን ያካትታል። ይህ ህንፃ ተገንብቶ ሲያልቅ አስተማማኝ መሰረተ ልማት፣ ፈጣን የኢንተርኔት ግንኙነት፣ ያልተቋረጠ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እና ዘመናዊ በውስጡ ለሚገኙ ሰራተኞች የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚያቀርብ ሲሆን፣ የሥራ ቅልጥፍናን፣ የሰራተኞችን ውጤታማነትና ዘላቂነት ያለው የእድገት አቅምን የሚደግፍ የሥራ ድባብን ይፈጥራል።

የፕሮጀክቱ የስነ-ሕንፃ (አርክቴክቸር) ዲዛይን በታዋቂዋ ኢትዮጵያዊት አርክቴክት እና የ RAAS አርክቴክቶች መስራችና ዋና አርክቴክት በሆኑት በራሄል ሻውል በሚመራው ቡድን የተዘጋጀ ሲሆን፣ የግንባታ ሥራው ደግሞ በኤልሚ ኦሊንዶ ኮንትራክተርስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እየተከናወነ ይገኛል።

ከ80 በላይ ዓለም አቀፍ ደንበኞችን የሚያገለግለው እና በስሩ ከ15,000 በላይ ሰራተኞችን የሚያስተዳድረው ሲሲአይ ግሎባል፣ የዚህ ፕሮጀክት ዋና ኦፕሬተር (Anchor Operator) ሆኖ ያገለግላል ተብሎ ይጠበቃል። በዛሬው እለት ከኢኢሆ ጋር የተፈራረሙት ስምምነትም ሲሲአይ ግሎባል በኢትዮጵያ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ከመደገፉም በላይ በኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን የ BPO ሥነ-ምህዳር ጠንካራ መሠረት የሚያስይዝ ነው።

“ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የቢፒኦ (BPO) ገበያ ያላትን እምቅ አቅም ወደ ተጨባጭ ኢንቨስትመንት፣ መሠረተ ልማትና የሥራ ዕድሎች ለመቀየር የሚያስችል ጠቃሚ እርምጃ ነው። በማለት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ በጉዳዩ ላይ የተናገሩ ሲሆን፤ ዶ/ር ብሩክ አክለውም “እንደ ኢኢሆ፣ ትኩረታችን ስትራቴጂካዊ ሀብቶችን በማንቀሳቀስ የውጭ ምንዛሪ ሊያስገኙ፣ ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ሊፈጥሩ እና በዓለም አቀፍ መድረክ ኢትዮጵያ ያላትን ቦታ  ሊያጠናክሩ ወደሚችሉ ኢንቨስትመንቶች ላይ መሳተፍ ነው። በዚህም መሰረት ከሲሲአይ ግሎባል ጋር ያደረግነው አጋርነት በኢትዮጵያ ውስጥ ሊስፋፋ የሚችል የ BPO ኢንዱስትሪ የመገንባት እና በዘርፉ ለተጨማሪ ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንትም የሚሆን መድረክ የመፍጠር አቅምም እንዳለን ያሳያል” ብለዋል።

የሲሲአይ ግሎባል ዋና ኦፐሬቲንግ ኦፊሰር ማርክ ቻና በበኩላቸው “ኢትዮጵያ ድንቅ የሰው ኃይል እና የዘርፉን ዕድል በደንብ የሚረዳ አመራር ያላት ሃገር ናት። ይህ የስምምነት ውል በዘርፉ ከኢትዮጵያ ጋር በቀጣይነት ለመስራት ያለንን ቁርጠኝነት የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ በዚህ ስምምነት አማካይነት ለደንበኞቻችን እና እዚህ ለሚሠሩ ወጣቶች ይዞት በሚመጣው ዕድል በእጅጉ ተደስተናል” ብለዋል።

ይህ አጋርነት የመጣው በሰሜን አሜሪካ፣ አውሮፓ እና ሌሎች ባደጉ ሃገራት የሚገኙ ኩባንያዎች ወጪ ቆጣቢ፣ ሊስፋፉ የሚችሉ እና በጂኦግራፊያዊ አቀማመጣቸው ምቹ የሆኑ የአገልግሎት መስጫ መድረኮችን በመፈለጋቸው ለBPO ያለው ዓለም አቀፍ ፍላጎት እየጨመረ በሄደበት ወቅት ነው። በዚሁ አግባብ ኢትዮጵያ በወጣት እና በተማረ የሰው ኃይሏ፣ በተወዳዳሪ የጉልበት ወጪዋ፣ በዜጎቿ የቋንቋ ችሎታ እና ከአውሮፓና መካከለኛው ምስራቅ ዋና ዋና ገበያዎች ጋር ባላት ስትራቴጂካዊ ቅርበት የተነሳ ለዘርፉ ሰፊ ዕድል ታቀርባለች።

ፕሮጀክቱ በመጀመሪያው ምዕራፍ 3,000 ገደማ የሥራ ዕድሎችን ይፈጥራል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የሥራ እንቅስቃሴው እየሰፋ ሲሄድ እና ወደ ሶስት ፈረቃ የሥራ ሞዴል ሲሸጋገር የሚፈጥረው የሥራ ዕድል እስከ 10,000 ይሆናል። በተጨማሪም የ BPO አገልግሎቶችን ለዓለም አቀፍ ገበያዎች በመላክ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የማስገኘት አቅም ይኖረዋል።

ከቀጥታ የሥራ ዕድል ፈጠራና እና ከውጭ ምንዛሪ ግኝት ባሻገር፣ ይህ ፕሮጀክት ለኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ዕድገት የበኩሉን አስተዋፅኦ የሚያበረክት፣ የሀገር ውስጥ የ BPO ባለሙያዎች ስብስብን የሚያጠናክር፣ ዓለም አቀፍ ኦፕሬተሮችን የሚስብ እና በዓለም አቀፍ የአገልግሎት እሴት ሰንሰለቶች ውስጥ ለላቀ ተሳትፎ ዕድሎችን የሚፈጥር ነው።

ለ ኢኢሆ ይህ ስምምነት ስትራቴጂካዊ ሀብቶችን የመክፈት፣ ዓለም አቀፍ ተቋማትን የመሳብ  እንዲሁም ካፒታልን፣ የሥራ ዕድልን፣ የውጭ ምንዛሪ ገቢና ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ እሴቶችን የመፍጠር አቅም ወደላቸው ዘርፎች በመግባት ተቋሙ የያዘውን ሰፊ የኢንቨስትመንት ፍላጎት የሚያንፀባርቅ ነው።

ይህ የፕሮጀክቱ  የመጀመሪያ ምዕራፍ ለወደፊቱ ማስፋፊያ መሠረት የሚጥል ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የ BPO ገበያ ያላትን ቦታ ስታጠናክር በቀጣይ ምዕራፎች አቅምን፣ የሥራ ዕድልን እና ኢንቨስትመንትን ያሳድጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ስለ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (ኢኢሆ) በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 487/2022 የተቋቋመ ድርጅት ነው። ኢኢሆ በስሩ የሚገኙ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን በሙያው በማስተዳደር፣ ከዓለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎች እና የድርጅት አስተዳደር መርሆዎች ጋር በማጣጣም ለዘላቂ የኢኮኖሚ ልማት አስተዋፅዖ ለማድረግ ያለመ ተቋም ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ስትራቴጂካዊ የኢንቨስትመንት ክንድ እንደመሆኑ መጠን፣ ለአሁኑ እና ለወደፊት ትውልድ የሚጠቅም እሴትን ለማሳደግ አስቦ የሚንቀሳቀስ ተቋም ነው።

Share:

More Posts

EIH and CCI Global Sign Agreement to Advance Ethiopia’s BPO Industry

Addis Ababa, Ethiopia —Ethiopian Investment Holdings (EIH), the strategic investment arm of the Government of Ethiopia, and CCI Global, Africa’s leading BPO operator, have signed

Ethiopia Launches $50 Million Mega-Refinery at Bole Lemi to Rewrite Regional Precious Metals Trade

Prime Minister Abiy Ahmed officially inaugurated the National Precious Metals Refinery today at the Bole Lemi Special Economic Zone. Established through a strategic partnership between

Ethiopia Enters East Africa’s Race for Regional Gold Trade With $50 Million Refinery

Ethiopia has entered the competition to capture a larger share of East Africa’s gold trade with the opening of its first refinery, a $50 million

Jaishankar meets Ethiopian Investments Holdings CEO, discusses deeper investment ties

External Affairs Minister Jaishankar on Sunday said he discussed ways to deepen investment partnerships between India and Ethiopia during a meeting with Brook Taye, CEO

PrevPreviousEIH and CCI Global Sign Agreement to Advance Ethiopia’s BPO Industry

Ethiopian Investment Holdings

Quick Links

  • Home
  • About Us
  • Investment
  • Portfolio
  • Contact Us

Contact

+251(0)111 70 45 40

info@eih.et

General Winget St, Hilcoe Building 5th floor, Addis Ababa ,Ethiopia

Copyright © 2025 All Right Reserved