• Home
  • About Us
    • Our Mission and Vision
    • Objectives
    • History
    • Board of Directors
    • Message From CEO
    • Our Leadership Team
  • Investment
    • Sectors We Invest In
    • How We Design Our Investments
    • How We Categorizes Our Investments
    • What Vehicles Does EIH Use?
    • Investment Considerations
    • Investment Process
    • EIH’s Value Proposition
    • Success Stories
  • Portfolio
    • Transport and Logistics
    • Energy and Connectivity
    • Financial Services
    • Mining, Engineering and Chemicals
    • Hospitality
    • Agriculture and Agro-Processing
    • Manufacturing
    • Trading
    • Construction and Real estate
  • Resources
    • Audit Report
    • Annual Report
    • Publications
    • Laws and Regulations
  • More
    • News and Media
    • Gallery
    • Career
    • Contact Us
qt=q_95

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በሚያስተዳድራቸው የልማት ድርጅቶች ውስጥ የሚነሱ የሙስናና የብልሹ አሰራር ጉዳዮችን ጥቆማ መቀበያ ድረ ገጽና መተግበርያ አዘጋጀ

  • January 1, 2026
  • Dagmawi Zeleke

ጋዜጣዊ መግለጫ

ታህሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በሚያስተዳድራቸው የልማት ድርጅቶች ውስጥ የሚነሱ የሙስናና የብልሹ አሰራር ጉዳዮችን ጥቆማ መቀበያ ድረ ገጽና መተግበርያ አዘጋጀ

የኢትዮጵያ መንግስት ስትራቴጂካዊ የኢንቨስትመንት ክንድ የሆነው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (ኢኢሆ) በሚያስተዳድራቸው የልማት ድርጅቶች ውስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ የሙስናና ብልሹ አሰራር ጉዳዮችን በቀላሉና ምስጢራዊነቱ በተጠበቀ መልኩ መቀበል የሚያስችል ድረ ገጽና መተግበርያ በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል።

ይህ ድረ ገጽና መተግበሪያ አደራ የተሰኘ ሲሆን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ግልጽነትን እና ተጠያቂነትን የሚያሰፍን መሳሪያ ሲሆን፣ በተለይ በመንግስት የልማት ድርጅቶች ውስጥ ያሉ ቋማት ውስጥ የሚኖሩ ብልሹ አሰራሮችን ለመቀነስ ያለው ሚና ከፍተኛ ነው ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህም በተጨማሪ ማንኛውም ግለሰብ (ሰራተኛ፣ ደንበኛ ወይም ተራ ተመልካች) ባሉበት ቦታ ሆነው በቀላሉ ጥቆማ እንዲሰጡ የሚያስችል፣ የጠቋሚውን ማንነት ሳይገልጹ (Anonymously) መረጃዎችን ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ የሚቀበልና በጽሁፍ ብቻ ሳይሆን በምስል፣ በድምጽ እና በሰነድ የተደገፉ ማስረጃዎችን በቀጥታ የሚቀበል ነው።

የኢኢሆ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ሃብታሙ ኃ/ሚካኤል በጉዳዩ ላይ እንዳሉት ከሆነ  “ሙስናና ብልሹ አሰራር የአንድን ሃገር እድል ያመክናል፣ ሃብትን ያባክናል፣ ተቋማትን ያዳክማል እንዲሁም ውጤታማነትን ይሸረሽራል።  ከግዜ ወደ ግዜ አይነቱንና መልኩን እየለዋወጠ የውጣውን ሙስናና ብልሹ አሰራርን በዘመናዊና ከግዜው ጋር የሚሄድን ዘዴ በመጠቀም ለመከላከል የሚያስችል አካሄድ መፍጠር ያስፈልጋል። ለዚህም ነው ይህንን አደራ የተሰኘው ድረ ገጽና መተግበርያ ለመፍጠር ያስፈለገው። አደራ በመደበኛው የደብዳቤ ወይም የሰው-ለሰው ግንኙነት የሚጠፋውን ጊዜ በመቀነስ፣ መረጃው በሰከንዶች ውስጥ ለሚመለከተው የክትትል ክፍል የሚያደርስ ሲሆን ሙስና ሳይከሰት ቀድሞ ለመከላከል ስለሚረዳ፣ ልማት ድርጅቶቻችን  ሊያጡ የሚችሉትን ከፍተኛ የሃብት ብክነትን በማዳን በኩል ያለው ጠቀሜታው እጅግ ከፍ ያለ ነው።” አቶ ሃብታሙ አክለውም  “በርካታ ሰዎች በአካል መጥተው በተቋሞች ላይ የሚያጋጥማቸውን የሙስናና ብልሹ አሰራር ለመጠቆም የሚያመነቱት ለደህንነታቸው በማሰብ ስለሆነ ይህንን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ያለምንም ስጋትና ፍራቻ በድፍረት ያሏቸውን መረጃዎች እንዲያጋሩ ያስችላል። አደራን ወደ ስራ በማዋላችን በኢትየጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስና በየልማት ድርጅቶቻችን ላይ የህዝብ እና የተገልጋየችን  እምነት ከማሳደግ አልፎ የሚመጡ ጥቆማዎችን በሲስተም ውስጥ ስለሚመዘገቡ መረጃዎች እንዳይጠፉወይም እንዳይበረዙ  የሚከላከል በመሆኑ ህብረተሰቡን የቁጥጥር ስርአቱ አካል በማድረግ የጋራ ጥበቃ ስሜትን የሚፈጥር ነው። በዚህም አካሄድ በተቋሞቻን ውስጥ ግልጽነንት፣ ታማኝነትንና ተጠያቂነት ለማስፈን ያለንን ቁርጠኝነትን እናረጋግጣለን”

ጥቆማ አቅራቢዎች ወደ https://adera.eih.et/ በመሄድ ማንነታቸውን ሳይገልጹ መረጃዎችን ደህነንታቸው በተጠበቀ መልኩ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን የሚመጡት ጥቆማዎችና መረጃዎችን የኢኢሆ ስራ አስፈጻሚዎች በተሰራላቸው ዳሽቦርድ አማካኝነት ስንት ጥቆማ ደረሰ? ስንቱ ተመረመረ እንዲሁም ምርመራው የደረሰበትን ሁኔታ ይከታተላሉ። ከዚህም በተጨማሪ የሙስናና ብልሹ አሰራር ጥቆማ አቀባበልን ከመደበኛው የወረቅት ስራ ወደ ዲጂታል ስርአት የሚያሽጋግረው ይህ ቴክኖሎጂ ኢኢሆ እነዚህን ችግሮችን ለመከላከል የሚወስደውን እርምጃ ያቀላጥፋል።

ስለ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ 

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ  (ኢኢሆ) በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 487/2022 የተቋቋመ ድርጅት ነው።  ኢኢሆ በስሩ የሚገኙ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን  በዘመናዊ መልኩ በመራትና በማስተዳደር፣  ከዓለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎች እና የድርጅት አስተዳደር መርሆዎች ጋር በማጣጣም ለዘላቂ የኢኮኖሚ ልማት አስተዋፅዖ ለማድረግ ያለመ ተቋም ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ስትራቴጂካዊ የኢንቨስትመንት ክንድ እንደመሆኑ መጠን፣ ለአሁኑ እና ለወደፊት ትውልድ የሚጠቅም እሴትን ለማሳደግ አስቦ የሚንቀሳቀስ ተቋም ነው::

Share:

More Posts

Effective Asset Management Boosts Revenue of Ethiopia’s Public Enterprises: EIH Deputy CEO

Revenue generated by public enterprises under Ethiopian Investment Holdings (EIH) has shown a significant increase due to improved asset management and efficient utilization, Deputy CEO

የመንግስት የልማት ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ተሻግረው በአፍሪካ ገበያ ተወዳዳሪ እና ተመራጭ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2018(ኢዜአ)፦ የመንግስት የልማት ድርጅቶች በኢኮኖሚ ውስጥ ያላቸውን አበርክቶ ይበልጥ በማጠናከር ከኢትዮጵያ ተሻግረው በአፍሪካ ገበያ ተወዳዳሪ እና ተመራጭ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰራ ‎መሆኑን የኢትዮጵያ

የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ከኪሳራ ወደ ትርፍ የቀየረው ጥበብ – ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)

EIH CEO Dr Brook Taye explains the journey of EIH since its establishment and its achievements at the Finance Forward Ethiopia Conference. View the full

Ethiopia, RUSAL Advance Plan for $1 Billion Aluminium Smelter as MoU Signed

Addis Ababa — Ethiopian Investment Holdings (EIH) has signed a Memorandum of Understanding (MoU) with RUSAL, one of the world’s largest producers of low-carbon aluminium, to

PrevPreviousEthiopia, RUSAL Advance Plan for $1 Billion Aluminium Smelter as MoU Signed
Nextየመንግስት የልማት ድርጅቶችን ከኪሳራ ወደ ትርፍ የቀየረው ጥበብ – ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)Next

Ethiopian Investment Holdings

Quick Links

  • Home
  • About Us
  • Investment
  • Portfolio
  • Contact Us

Contact

+251(0)111 70 45 40

info@eih.et

General Winget St, Hilcoe Building 5th floor, Addis Ababa ,Ethiopia

Copyright © 2025 All Right Reserved