• Home
  • About Us
    • Our Mission and Vision
    • Objectives
    • History
    • Board of Directors
    • Message From CEO
    • Our Leadership Team
  • Investment
    • Sectors We Invest In
    • How We Design Our Investments
    • How We Categorizes Our Investments
    • What Vehicles Does EIH Use?
    • Investment Considerations
    • Investment Process
    • EIH’s Value Proposition
    • Success Stories
  • Portfolio
    • Transport and Logistics
    • Energy and Connectivity
    • Financial Services
    • Mining, Engineering and Chemicals
    • Hospitality
    • Agriculture and Agro-Processing
    • Manufacturing
    • Trading
    • Construction and Real estate
  • Resources
    • Audit Report
    • Annual Report
    • Publications
    • Laws and Regulations
  • More
    • News and Media
    • Gallery
    • Career
    • contact-us
qt=q_95

ኢትዮጵያና ጅቡቲን የሚያገናኝ የነዳጅ መሰረተ ልማት ግንባታን የሚያስጀምር የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ፤ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስም የግንባታ ስራውን ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

  • September 24, 2026
  • Dagmawi Zeleke

ጅቡቲ፣ መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም. — ከኢትዮጵያ እስከ ጅቡቲ የሚዘረጋና ሁለቱን ሃገራት የሚያገናኝ የነዳጅ ማከማቻና የማስተላለፊያ መስመር መሰረተ ልማትን ግንባታ መጀመርን የሚያበስር የመሰረት ድንጋይ በዛሬው እለት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ በጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ክቡር እስማኤል ዑመር ጌሌ እና በዳንጎቴ ግሩፕ ፕሬዝዳንት አልሃጂ አሊኮ ዳንጎቴ አማካኝነት ተቀምጧል።

ይህ ታሪካዊ መሰረተ ልማት በጅቡቲ ከሚገኙ የባህር ላይ ነዳጅ መቀበያ እና ማከማቻ ተቋማት የሚራገፈውን ነዳጅ በሚዘረጉት ማስተላለፊያ መስሮች አማካይነት ኢትዮጵያ ከሚገኙ ከማከማቻ እና ከማከፋፈያ መሰረተ ልማቶች ጋር የሚገናኝ ሲሆን፣ የተቀናጁ የነዳጅ ምርቶችን ወደ ኢትዮጵያ በቀላሉ በማስተላለፍ የተቀላጠፈ የአቅርቦት ሰንሰለትን ይፈጥራል።

የመሰረተ ልማቱን ግንባታ ለማከናወን የኢትዮጵያ መንግስት የስትራቴጂካዊ የኢንቨስትመንት ክንድ የሆነው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (ኢኢሆ)፣ ዳንጎቴ ኢንዱስትሪስ ሊሚትድ እና ግሬት ሆርን ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ መካከል በዛሬው እለት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ይህ ፕሮጀክት ለቀጠናው ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ዕድል የሚፈጥር ሲሆን፣ ዋና ዋና የሎጂስቲክስ ማነቆዎችን የማስወገድ፣ የነዳጅ ምርት አቅርቦት ተመጣጣኝነትና ውጤታማነትን የማሻሻል፣ የትራንስፖርት ወጪን የመቀነስ እና የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እድገትን የሚደግፍ ነው።

በተጨማሪም ይህ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ ከጅቡቲ ጋር ያላትን ትስስር በማጠናከር፣ ለላቀ ቀጠናዊ ውህደት እና ተወዳዳሪነት አስተዋፅኦ የሚያበረክት ነው። የማስተላለፊያ መስመሩ የነዳጅ አጠቃቀምን በማሳደግ ከዚህ ቀደም ከተለመደው ነዳጅን በየብስ ትራንስፖርት አማካኝነት ብቻ የማስተላለፍን ጥገኝነትን የመቀነስ እና ከዘርፉ ጋር የተያያዘውን የካርቦን አሻራ (carbon footprint) የመቀነስ አቅም አለው።

 “የኢትዮጵያን የነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለት ለማጠናከር፣ ቀጠናዊ ትስስርን ለማሻሻል እና ሀገራችን ያላትን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ይህ ፕሮጀክት ይዞት የሚመጣው ዕድል ትልቅ ነው” በማለት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ  በጉዳዩ ላይ የተናገሩ ሲሆን ዶ/ር ብሩክ አክለውም “እንደ ኢኢሆ፣ ትኩረታችን ወሳኝ መሰረተ ልማቶችን በሚያጠናክሩ እና የረጅም ጊዜ እሴትን በሚፈጥሩ ኢንቨስትመንቶች ላይ እንደመሆኑ ይህ ዛሬ የተፈራረምነው የመግባቢያ ስምምነትና ስራውን ለማስጀመር የተጣለው የመሰረት ድንጋይ የምንጀምረው ስራ የአቅርቦት ውጤታማነትን ለማሻሻል፣ ቀጠናዊ ውህደትን ለማጥበቅ እና የትራንስፖርት ዘርፉን ለመደገፍ ትልቅ አቅም ያለው ነው” ብለዋል።

የዛሬው ስምምነት በኢኢሆ እና በዳንጎቴ ግሩፕ መካከል እያደገ የመጣውን የኢንቨስትመንት ቁርኝት የሚያጠናክር ሲሆን፣  ከዚህ ቀደም በጎዴ በሚገኘው እና በዓመት ሶስት ሚሊዮን ቶን የማምረት አቅም ባለው በ2.5 ቢሊዮን ዶላር የዩሪያ ማዳበሪያ ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታ ላይ አብረው ለመስራት የጀመሩት ስራ የሚታወስ ነው።

ይህ የኢንቨስትመንት መጠኑ 660 ሚሊየን ዶላር የሚሆንና ግንባታው ከተጀመረ በሁለት አመታት ባልሞላ ግዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ የታቀደው ፕሮጀክት ወሳኝ መሰረተ ልማቶችን ለማጠናከር፣ ቀጠናዊ ትስስርን ለማሻሻል እና የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ ውህደት ከቀጠናው ጋር ለመደገፍ የሚደረገውን ሰፊ ጥረት የሚያንፀባርቅ ነው።

ስለ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ  (ኢኢሆ) በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 487/2022 የተቋቋመ ድርጅት ነው።  ኢኢሆ በስሩ የሚገኙ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን  በሙያው በማስተዳደር፣  ከዓለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎች እና የድርጅት አስተዳደር መርሆዎች ጋር በማጣጣም ለዘላቂ የኢኮኖሚ ልማት አስተዋፅዖ ለማድረግ ያለመ ተቋም ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ስትራቴጂካዊ የኢንቨስትመንት ክንድ እንደመሆኑ መጠን፣ ለአሁኑ እና ለወደፊት ትውልድ የሚጠቅም እሴትን ለማሳደግ አስቦ የሚንቀሳቀስ ተቋም ነው::

Share:

More Posts

Ethiopia Launches $50 Million Mega-Refinery at Bole Lemi to Rewrite Regional Precious Metals Trade

Prime Minister Abiy Ahmed officially inaugurated the National Precious Metals Refinery today at the Bole Lemi Special Economic Zone. Established through a strategic partnership between

Ethiopia Enters East Africa’s Race for Regional Gold Trade With $50 Million Refinery

Ethiopia has entered the competition to capture a larger share of East Africa’s gold trade with the opening of its first refinery, a $50 million

Jaishankar meets Ethiopian Investments Holdings CEO, discusses deeper investment ties

External Affairs Minister Jaishankar on Sunday said he discussed ways to deepen investment partnerships between India and Ethiopia during a meeting with Brook Taye, CEO

Addis Ababa: Jaishankar Meets Ethiopian Investments Holdings CEO

Addis Ababa: External Affairs Minister S. Jaishankar meets Brook Taye, Chief Executive Officer of Ethiopian Investment Holdings, in Addis Ababa, Ethiopia, on Saturday, October 10,

PrevPreviousFoundation Stone Laid as EIH Signs MoU for Transformative Petroleum Infrastructure Connecting Ethiopia and Djibouti
NextAfrica’s richest man and Ethiopia to lay $660 million fuel lifeline, giving the landlocked country a new fuel routeNext

Ethiopian Investment Holdings

Quick Links

  • Home
  • About Us
  • Investment
  • Portfolio
  • Contact Us

Contact

+251(0)111 70 45 40

info@eih.et

General Winget St, Hilcoe Building 5th floor, Addis Ababa ,Ethiopia

Copyright © 2025 All Right Reserved